Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dcoz

DC Office of Zoning
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

የድርጅቱ ስም : ዲ.ሲ. የክልል ቢሮ

የድርጅቱ ዓላማ:
የዲ.ሲ. የክልል ቢሮ (DCOZ) ዓላማ የክልል ኮሚሲዮን (ZC) እና የክልል ቁጥጥር ቦርድ (BZA) በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የክልል ጉዳይን በተመለከተ ለሚያደርጉት ክትትል የአስተዳደር፣ የሙያ እና የቴክኒካል እርዳታ መስጠት ነው።

ዋና ፕሮግራሞች/የክፍሎች ገለጻ:     

የዲ.ሲ. የክልል ቢሮ (DCOZ) ለክልል ኮሚሲዮን (ZC) እና ለክልል ቁጥጥር ቦርድ (BZA) የክልል ማመልከቻዎች አሠራር ሂደትን ይቆጣጠራል። ድርጅቱ ማመልከቻዎችን ተቀብሎ ይመረምራል፣ የተወሰኑ የክልል መስፈርቶች መሟላታቸውን ለመገምገም የቀጠሮ ቀኖች ይወስናል፣ በቆይታ ላይ ያሉ ጉዳዮችን ለማስወስን ስብሰባ ያዘጋጃል እና የሕግ ትዕዛዞችን ያስተላልፋል። ይህንን ሂደት ጉልህና ውጤታማ ለማድረግ ቴክኖሎጂ ታላቅ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም የዲ.ሲ. የክልል ቢሮ (DCOZ) የኮሎምብያ ዲስትሪክት ዜጎች ስለ ክልል ማመልከቻ ሂደት ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስተባብራል።

የትርጉም አገልግሎቶች:

በክልል ኮሚሲዮን (ZC) እና በክልል ቁጥጥር ቦርድ (BZA) ችሎቶች ወይም ስብሰባዎች ላይ ለመካፈል ወይም ከዲ.ሲ. የክልል ቢሮ (DCOZ) ጋር ለመገናኘት የትርጉም አገልግሎት የሚፈልጉ ሰዎች ዶ/ር ፍሬድሪክ ኬንድሪክን በስልክ ቁጥር (202) 727-0312፣ በኢሜል [email protected] ወይም በቢሮ አድራሻ 441 4th Street, NW, Suite 200-S, Washington, 20001 ከጠዋቱ ሶስት ሳዓት ተኩል እስከ ምሽቱ አሥራአንድ ስዓት መጠየቅ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ድርጅታችን ስለሚሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች በድህረ ገጻችን http://dcoz.dc.gov/ “የክልል መፅሄት በሌሎች ቋንቋዎች” በሚለው አርዕስት ሥር ይገኛል። መፅሄቱ ስድስቱንም ቋንቋዎች በደማቃ ቀለሞች ስለሚያመለክት በደንብ ይታያል።

የዞን ክፍፍል ይግባኝ አቤቱታዎች፡

የዞን ክፍፍል ማሻሻያ ቦርዱ በይግባኝ አቤቱታ አቅራቢው በየትኛውም ትዕዛዝ፣ መስፈርት፣ ውሳኔ፣ ቁርጠኝነት ወይም በዞን ክፍፍል አስተዳዳሪ ወይም ማንኛውም የአስተዳደር ኃሊፊ ወይም አካል የተፈፀመ እምቢተኝነት መኖሩን በሚጠይቅ ጊዜ በዞን ክፍፍል ደንቦች አስተዳደር ወይም አፈፃፀም ሊይ የይግባኝ አቤቱታዎችን በማድመጥ ይወስናል።
የዞን ክፍፍል ማሻሻያ ቦርዱ ትዕዛዙ፣ መስፈርቱ፣ ውሳኔው፣ ቁርጠኝነቱ ወይም እምቢተኝነቱ ሙለ በሙለ ወይም በከፊል በማንኛውም የዞን ክፍፍል ወይም ካርታ ሊይ ያልተመሰረተ ከሆነ፣ ማንኛውንም ይግባኝ ወይም የይግባኝ ክፍል የማድመጥ እና የመወሰን ስልጣን የሇውም።
የዞን ክፍፍል ይግባኝ አቤቱታዎችን የመስማት ስልጣኑን ከመተግበር አኳያ፣ የዞን ክፍፍል ማሻሻያ ቦርዱ ትዕዛዙን፣ መስፈርቱን፣ ውሳኔውን፣ ቁርጠኝነቱን ወይም ይግባኝ የተባሇበትን እምቢተኝነት ሙለ በሙለ ወይም በከፊል፣ ሉያጸና ወይም ሉቀሇብስ፣ ወይም ውሳኔውን ወይም ፈቃዱን ሇማስፈጸም አስፈሊጊ ሉሆን የሚችል ትዕዛዝ ሉያሳልፍ ይችሊል፣ በዚህም ይግባኙ የመጣበት መኮንን ወይም አካል ሙለ ስልጣን ይኖረዋል።
የይግባኝ አቤቱታ አቅራቢው ይግባኙ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አሇበት። ጉዳዩን በተቃራኒ መንገድ የሚደግፍ ማስረጃ ካልቀረበ፣ የይግባኝ አቤቱታ አቅራቢው ከዚህ ግዴታ ነጻ አይሆንም።

ተልእኮ

የDC የዞኒንግ ቢሮ (DCOZ) ተልእኮ  ለዞኒንግ ኮሚሽን (Zoning Commission, ZC) እና ለዞኒንግ አጀስትመንት ቦርድ (Board of Zoning Adjustment, BZA)  በColumbia (ኮሎምቢያ) ግዛት ውስጥ ያሉ የዞኒንግ ጉዳዮችን በመቆጣጠር እና ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት ላይ አስተዳደራዊ፣ ሞያዊ፣ እና የቴክኒካል ድጋፍ መስጠት ነው።

የአገልግሎቶች አጭር መግለጫ

DCOZ የZC እና BZA  የዞኒንግ የማመልከቻ ሂደትን ያስተዳድራል። ኤጄንሲው ማመልከቻዎችን ይመረምራል እና ይቀበላል፣ ጉዳዮች የተለዩ የዞኒንግ መስፈርት የሚያሟሉ መሆኑን ለመወሰን የአቤቱታ መስሚያ ቀናትን ቀጠሮ ይይዛል፣ በቀጠሮ ላይ ያሉትን ማመልከቻዎች ላይ ውሳኔ ለመወሰን የስብሰባ ቀጠሮ ይይዛል፣ እና ህጋዊ ትእዛዞችን ይሰጣል።  ውጤታማነት እና ግልጽነት እንዲጨምር በማድረግ ቴክኖሎጂ ይህን ሂደት ለመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በተጨማሪ DCOZ የColumbia (ኮሎምቢያ) ግዛት ዜጋዎች የዞኒንግ ማመልከቻ ሂደቱ ላይ ተጨባጭ የሆነ ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የተደራሽነት ተግባርን በግንባር ቀደምትነት ያከናውናል።

የዞኒንግ ሂደት

በColumbia (ኮሎምቢያ) ግዛት ውስጥ ግንባታ ለማካሄድ፣ ወይም ባሉ ህንጻዎች ላይ ጥገናዎችን፣ ማሻሻያዎችን፣ ወይም ጭማሬዎችን ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት የታቀደው ፕሮጀክት የሚመለከተውን የዞኒንግ መስፈርቶች ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ለመወሰን የተገልጋይ እና የቁጥጥር ጉዳዮች ዲፓርትመንትን(DCRA)  ማማከር አለባቸው።  የታቀደው ፕሮጀክት ከዞኒንግ ደምቦች ወይም የዞኒንግ ካርታ ጋር የሚጋጭ ከሆነ፣ የDCRA አካል የሆነው እና በዞኒንግ ኮሚሽን (Zoning Commission, ZC) የወጡትን የዞኒንግ ደምቦችን ለመተርጎም ስልጣን ያለው የዞኒንግ አስተዳደሩ (Zoning Administrator, ZA) ፣ የሚያስፈልገውን የዞኒንግ መፍትሄ ይወስናል።  ግለሰቡ ወይም ድርጅቱ በዚያን ጊዜ የሚከተሉትን ሊያደርጉ ይችላሉ፣ (1) ከዞኒንግ ደንቦች እና የዞኒንግ ማፕ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የታቀደውን ፕሮጀክት ማሻሻል፣ (2) የZA ውሳኔን (ተገቢ ምክንያት ሲኖር) BZA ጋር ይግባኝ መጠየቅ ፣ ወይም (3) ከZC ወይም ከBZA ዳኝነት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

የዞኒንግ ደምቦችን ወይም የዞኒንግ ካርታ፣ የአየር መብቶችን ማቋቋም፣ ወይም የታቀደ የክፍል ልማትን (Planned Unit Development, PUD) ማሻሻልን በሚመለከት ተገቢ መፍትሄ ለማግኘት ከZC ተቀባይነት ማግኘትን ይጠይቃል፣ በሌላ በኩል ልዩነቶች፣ ልዩ ምክንያቶች፣ እና ዞኒንግ በሚመለከት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ይግባኞች በዋነኝነት በBZA የሚታዩ ናቸው።  BZA በተጨማሪ በተወሰኑ ድብልቅ የከተማ ስፍራዎች ላይ በሚገኙ የታቀዱ የቻንሰሪ ተቋማት ልማት እቅዶችን ልዩ ግምገማ ያካሂዳል።

አድራሻ:
Office of Zoning
One Judiciary Square
441 4th Street NW / Suite 200S
Washington, DC 20001
(202) 727-4294
dcoz.dc.gov