Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dcoz

DC Office of Zoning
 
Welcome to the Office of Zoning

ቨርችዋል የህዝብ ችሎት

ቨርችዋል የህዝብ ችሎት

የህዝብ ችሎቶቹን እንዴት ማየት እና መሳተፍ እንደሚቻል መረጃ።

የዞኒንግ ኮሚሽን (ZC) እና የዞኒንግ ማስተካከያ ቦርድ (BZA) ቨርችዋል የህዝብ ስብሰባዎች እና ችሎቶች እያካሄዱ ነው። በቨርችዋል የህዝብ ችሎቶች ምስክሮች በአካል አይሰሙም፣ ነገር ግን ቀጠሮ በተያዘላቸው የትኛውም የህዝብ ችሎቶች ላይ አስተያየቶችን መስጠት ወይም መመስከር የሚችሉበት አማራጭ መንገዶች አሉ፤

  • የምስክርነት ቃልን በጽሁፍ ማቅረብ
    • የኢንተራክቲቭ ዞኒንግ መረጃ ሲስተምን በመጠቀም በ https://app.dcoz.dc.gov/Login.aspx
    • ኢሜይል በማድረግ ለ [email protected] ለ BZA ወይም [email protected]ለ ZC.
  • በ WebEx ቪዲዮ፣
    • ለመመስከር ከታች ይመዝገቡ፣ እና የዞኒንግ ቢሮ (OZ) ወደ WebEx እንዴት እንደሚገቡ መመሪያዎችን ኢሜይል ያደርግልዎታል።
  • በስልክ፣
    • ለመመስከር ከታች ይመዝገቡ፣ እና የህዝብ ችሎት ጋር እንዴት መደወል እንደሚችሉ የሚገልጽ መመሪያዎችን P[ ኢሜይል ያደርግልዎታል፤ እና
    • ለምስክርነት ለመመዝገብ እና የስልክ ጥሪ መረጃ ለማግኘት ወደሚከተሉት የP[ ሠራተኞች ይደውሉ፣
      • ZC: Ella Ackerman (ሮን ባሮን) በ (202) 727-0789    
      • BZA: Robert Reid (ሮበርት ሪድ) በ (202) 727-5471

ለምስክርነት ይመዝገቡ፣

በ WebEx ቪዲዮ እና በስልክ አማካኝነት የሚመሰክሩ ምስክሮች ከህዝብ ችሎቱ 24 ሰዓት ቀደም ብለው ለምስክርነት እንዲመዘገቡ በጥብቅ ይመከራሉ። ከችሎቱ 24 ሰዓት በፊት ካልተመዘገቡ፣  እርስዎ የ OZ የስልክ መስመር ጋር በ (202) 727-5471 ወደ BZA እና በ(202) 727-0789 ወደ ZC በመደወል ለምስክርነት መመዝገብ እና ወደ WebEx የመገቢያ ወይም ስልክ የመደወያ መመሪያዎችን ማግኘት አለብዎ።

የጽሁፍ የምስክርነት ቃል፣

ZC እና BZA ሁሉም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን በጽሁፍ እንዲያዘጋጁ፣ የምስክርነት ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት የጽሁፍ የምስክርነት ቃሉን እንዲያስገቡ፣ እና በቃል የሚያቀርቡትን የማጠቃለያ ሀሳቦች እንዲገድቡ ይጠይቃል። ZC እና BZA ውሳኔ መስጠት ያለባቸው የቀረበላቸውን ሪከርድ(ማስረጃ) መሠረት በማድረግ ነው፣ ስለዚህ  ሁሉም የጽሁፍ አስተያየቶች እና/ወይም የምስክርነት ቃል ከችሎት ቀጠሮው ቢያንስ 24 ሰዓት በፊት ከመዝገቡ ጋር መያያዝ አለበት።

እንደ ምስክርነት አካል ተቆጥሮ ሊቀርብ ከማይገባው ከ“ላይቭ” ቪዲዮ ውጪ --የጽሁፍ የምስክርነት ቃል ወይም ተጨማሪ ደጋፊ ሰነዶችን በንዑስ ርዕስ Y እና Z § 103.13 መሠረት በኦንላይን ቨርችዋል ችሎት ወቅት በማስረጃነት ለማያያዝ መጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ የሚቻለው፣

  1. ኤግዝቢቱን ለማቅረብ የሚጠይቀው ሰው የሚከተለውን ካብራራ፣
    1. እንዲያያዝ የሚጠየቀው ኤግዝቢት አስፈላጊነት፣
    2. ጠያቂው በንዑስ ርዕስ Y § 206 መሠረት ኤግዝቢቱን ከችሎት ቀኑ በፊት ያላያያዘበትን ምክንያት ጨምሮ፣ ማስረጃው እንዲያያዝ የሚፈቀድበት በቂ ምክንያት መኖሩን፤ እና
    3. እንዲቀርብ የተጠየቀው ኤግዝቢት ማንኛውም ወገን ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ተጽዕኖ እንደማያሳድር ማሳየት።

የጊዜ ገደቦች፣

በቃል ምስክርነት የሚሰጥበት የሚከተለው ከፍተኛ የጊዜ ገደቦች መከበር አለባቸው እና ከዚያ ጊዜ በላይ ማለፍ የለበትም፤

  • ድርጅቶች     እያንዳንዳቸው 5 ደቂቃ
  • ግለሰቦች          እያንዳንዳቸው 3 ደቂቃ

ሁሉንም የህዝብ ችሎቶች በ Webex ወይም በ  YouTube Live መመልከት ይቻላል እና ከችሎቱ በኋላ ቪዲዮን በጥያቄ ማግኘት ይቻላል።

ልዩ አቅርቦቶች ወይም የቋንቋ እርዳታ አገልግሎቶች የሚያስፈልግዎ ከሆነ (የጽሁፍ ትርጉም ወይም የቃል ትርጉም)፣ እባክዎ Zee Hill በ (202) 727-0312 ወይም [email protected] ቢያንስ ከቀጠሮው አምስት ቀናት በፊት ያግኙ። እነዚህ አገልግሎቶች የሚሰጡት ከክፍያ ነጻ ነው።

ስለ ቨርችዋል ምስክርነት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ  Virtual Hearing FAQs(የቨርችዋል ችሎት አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶች ይመልከቱ።

 

     ለመመስከር ይመዝገቡ    >